የካርድ አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ

ካርድ ታኅሣሥ 3፣ 2014 በተከናወነ የሰብዓዊ መብቶች ፌስቲቫል፣ በ10 ዙር ሲያሠለጥናቸው የነበሩ 364 የአዲስ አበባ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎችን "አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ" በሚል ሰይሟል።

ካርድ ከተለያዩ የመንግሥት እና የግል ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በፍላጎታቸው መሠረት ሲመለምላቸው የነበረውን ተማሪዎች በሰብዓዊ መብቶች ፅንሰ ሐሳብ፣ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት፣ የመሰብሰብ እና የመደራጀት መብቶችን እንዲሁም የስርዓተ ፆታ እኩልነትን የሚያስገነዝቡ ሥልጠናዎችን አቅርቦላቸዋል።

ከሥልጠናው በኋላ፣ ተማሪዎቹ በየትምህርት ቤቶቻቸው ከሰብዓዊ መብቶች ጋር የተገናኙ ክለቦችን እንዲፈጥሩ ካርድ የማበረታቻ ሥራዎችን እየሠራ ይገኛል። በፌስቲቫሉ ላይ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን ኮሚሽነር ዶ/ር ዳንኤል በቀለ ሲሆኑ፣ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰብሳቢ ክብርት ብርቱካን ሚደቅሳ ከሠልጣኞቹ ጋር የጥያቄ እና መልስ ቆይታ አድርገዋል።

በተጨማሪም፣ የተለያየ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች መሪዎች ለአዲሱ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ ልምዳቸውን አጋርተዋል። ልምዳቸውን ያካፈሉት መሪዎች አምሃ መኮንን ከጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች፣ ያሬድ ኃይለማርያም ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል፣ እና ማሕሌት ዘለቀ ከሴቶች የኢኮኖሚ ማብቃት አፍሪካ ናቸው። መሪዎቹ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት መሪነት የሚጠይቀውን ሥራ እና ያሉበትን ፈተናዎች አስረድተዋል።

ከአዲሱ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ አባላት መካከል የተመረጡ ተማሪዎች ወደ መድረክ በመውጣት ለታዳሚዎቹ ወደ ሥልጠናው እንዴት እንደገቡ፣ ከሥልጠናው በኋላ በየማኅበረሰቦቻቸው ምን እየሠሩ እንደሆነ እና ምን ዕቅድ እንዳላቸው ተናግረዋል። በከሰዓቱ የፌስቲቫሉ መርሐ ግብር፣ ከሠልጣኞቹ መካከል በቅድመ ፈተና የተመረጡ 10 ተመሪዎች ለጥያቄ እና መልስ ውድድር ቀርበው ሦስቱ ተሸላሚ ሆነዋል።

የሥልጠና ፕሮግራሙ ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ትምህርት ቤቶችን በማካተት በሚቀጥሉት ዓመታትም ይካሔዳል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.