Skip to main content

ሰላም ይስበኩ፤ ይሸለሙ!

መግቢያ

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድከሜታ ጋር በመተባበር ፈጠራ በተሞላበት መንገድ የሰላም መልዕክት አዘጋጅተው በማጋራት በርካታ ምላሽ ያገኙ የፌስቡክና ኢንስታግራም ተጠቃሚዎችን ለመሸለም ዝግጅቱን አጠናቅቋል። አሸናፊዎች ከ50 ሺሕ እስከ 100 ሺሕ ብር ድረስ ይሸለማሉ።

ከተሳታፊዎች የሚጠበቀው በኢንፎግራፊክስ፣ አኒሜሽን፣ ፎቶ፣ ወይም ቪዲዮ ያዘጋጁት ፈጠራ የተመላበት የሰላም መልዕክት #ሰላምለኢትዮጵያ ወይም #Peace4Ethiopia ከሚል ሀሽታግ ጋር ከሕዳር 5 እስከ ኅሣሥ 21 ባሉት ቀናት ውስጥ በፌስቡክ ወይም ኢንስታግራም ማጋራት ነው። ብዙ ምላሽ በማግኘት ከአንድ (1) እስከ ሦስት (3) የወጡ ተሳታፊዎች የ50ሺ፣ የ75 ሺሕ፣ እና የ100ሺሕ ብር ሽልማቶች ያገኛሉ፤ በተጨማሪም ሥራዎቻቸው ለብዙኃን ተደራሽ እንዲሆኑ በካርድ የፌስቡክ ገጽ ፕሮሞት ይደረጋል።

ዓላማ

የሰላም መልዕክት ውድድሩላማ ኢትዮጵያውያን የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ስለ ሰላም ፈጠራ በተሞላበት መንገድ ውይይት እንዲያደርጉ እና መልዕክቶቻቸውን እንዲለዋወጡ ማድረግ ነው። 

የውድድሩ መስፈርት

ተሳታፊዎች በዚህ ውድድር ውስጥ ተቀባይነት ለማግኘት፣ 

  1. ከዚህ ቀደም በማኅበራዊ ሚዲያዎች ላይ የጥላቻ ንግግሮችን የማስተላለፍ ታሪክ የሌላቸው እና የአመፅ ቀስቃሽ ጽሑፎችን ጽፈው ወይም አጋርተው የማያውቁ መሆን አለባቸው፤
  2. ወጥ ወይም ከሌሎች ሰዎች ፈጠራ ያልተኮረጀ ሥራ ማቅረብ አለባቸው፤ 
  3. የኢንፎግራፊክስ፣ የአኒሜሽን፣ የፎቶ፣ ወይም የቪዲዮ መልዕክቶቻቸውን ራሳቸው በሚጠቀሙበት የፌስቡክ ወይም የኢንስታግራም መድረኮች፣ #ሰላምለኢትዮጵያ ወይም #Peace4Ethiopia, #CARDEthiopia ከሚሉ ሀሽታጎች ጋር ማጋራት አለባቸው፤
  4. የኢንፎግራፊክስ፣ የአኒሜሽን፣ የፎቶ፣ ወይም የቪዲዮ መልዕክቶቻቸውን ከሕዳር 5 (November 15) እስከ ታኅሣሥ 21፣ 2016 (December 31, 2023) ባለው ጊዜ ውስጥ ማጋራት አለባቸው።
  5. ተሳታፊዎች የትኛውንም የአገር ውስጥ ቋንቋ መጠቀም ይችላሉ።

የአሸናፊዎች መረጣ

የውድድሩ ሦስት አሸናፊዎች የሚመረጡት 1ኛ) የሰላም መልዕክት የሆነ ወጥ (ኦሪጅናል) ይዘት ሠርተው ፌስቡክ ወይም ኢንስታግራም ላይ ያጋሩ፣ 2ኛ) #ሰላምለኢትዮጵያ ወይም #Peace4Ethiopia የሚለውን ሀሽታግ የተጠቀሙ፣  3ኛ) ብዙ የተወደደ (likes and reactions) ያገኙ ይዘቶች ይሆናሉ።

Share this post

Comments (0)

Add new comment

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.