ካርድ በዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ግጭት ጉዳይ ለደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ሥልጠና ሰጠ

Debre-berhan

ካርድ፣ ‘ከናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዲሞክራሲ’ በተደረገ ድጋፍ ሰጪነት ለደብረ ብርሃን ዩንቨርሲቲ ተማሪዎች ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ በውይይት እንዴት መፍታት እንዳለባቸው ታኅሣሥ 18 እና 19 ፣ 2012 በደብረ ብርሃን ከተማ፣ ኢትዮ በርኖስ ሆቴል ሥልጠና ሰጠ። በሥልጠናው ላይ 20  የተለያዩ ክለብ እና ማኅበራት መሪዎች የሆኑ ተማሪዎች ተሳትፈዋል። የዚህ ሥልጠና ዓላማ ተማሪዎች ግጭትን ለመከላከልና በንግግር ለመፍታት ክህሎታቸውን እንዲያዳብሩ መርዳት ነው። 

የመጀመሪያውን ቀን  ሥልጠና የተሰጠው “በብዝኀነት አስተዳደር” ጉዳይ የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እየሠሩ ባሉት መስፍን ማናዜ ሲሆን፥ ትኩረቱም ዋና ዋና ግጭቶችና የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ማስተዋወቅ፣ የግጭት መንስዔዎችና ውጤት  እንዲሁም በዩኒቨርሲቲዎች ግጭት ሲነሳ በንግግር እንዴት መፍታት ይቻላል የሚሉት ላይ ያጠነጥናል።።  መስፍን ማናዜ ከላይ ሥልጠናውን  በኢትዮጵያ ውስጥ ከዩኒቨርሲቲዎች ነባራዊ አሠራር ጋር በማያያዝ ሰተዋል።

የሁለተኛው ቀን ሥልጠና በበፍቃዱ ኃይሉ (የካርድ ዋና ዳይሬክተር) እና አጥናፉ ብርሃኔ (የካርድ የፕሮግራም ዳይሬክተር) ተሰጥቷል። የሁለተኛው ቀን ሥልጠና ትኩረት ስለ ሰብአዊ መብቶች ምንነት፣ ሐሳብን በነጻነት መግለጽ እና ሕጋዊ ወሰኖቹ ብሎምየተዛቡ መረጃዎችን እና የጥላቻ ንግግሮችን መከላከል ላይ የሚያጠነጥን ነበር። 

ተመሳሳይ ሥልጠናዎችለአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ተሰጥቷል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.