ካርድ በፀረ-ጥላቻ ንግግር ረቂቅ አዋጁ ዙሪያ የምክክር መድረክ አዘጋጀ

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ቅዳሜ፣ ታኅሣሥ 4፣ 2012 ባካሔደው የምክክር መድረክ የበይነመረብ ላይ ጸሐፊዎችን በፀረ ጥላቻ ንግግር እና የሐሰተኛ መረጃዎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በወጣው ረቂቅ አዋጅ ላይ አወያየ። የምክክር መድረኩ ከሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት እና ከፌዴራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ የተወከሉ ተሳታፊዎችም ተገኝተውበታል።
በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ መምህር የሆኑት መሰንበት አሰፋ (ዶ/ር) የውይይት መድረኩን የመሩት ሲሆን፣ የሐሳብን የመግለጽ ነጻነትን እና ሕጋዊ ተቀባይነት ያላቸው ገደቦች ላይ ዓለማቀፍ ሕግጋት እና ዐውዱ ምን እንደሚመስል አስረድተዋል። በማስከተልም፣ ከተሳታፊዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች መልሶቻቸውን ሰጥተዋል።
በተጨማሪም፣ ተሳታፊዎች በረቂቅ አዋጁ ላይ ያሏቸውን ጥያቄዎች ያነሱ እና የተወያዩ ሲሆን የምክርቤቱ እና የዐቃቤ ሕግ ተወካዮች የተሳታፊዎቹን ጥያቄዎች ለሚወክሏቸው ተቋማት እንደሚያደርሱ ቃል ገብተዋል። የብዙዎቹ ተሳታፊዎች ጥያቄ የረቂቅ አዋጁ ዓላማ ምንድን ነው ከሚል ጥርጣሬ የመነጨ ነው።
Add a review