መፍትሔው ዴሞክራሲ ነው! ዲሞክራሲን ይጠብቁ - መጪውን ጊዜ ያሳምሩ!

ችግሩ ምንድነው?

በሽግግርላይ ያሉ ወይም የዴሞክራሲን ግብ ያደረጉ ማኅበረሰቦች በአንድ ጊዜ ምላሽ ለመስጠት እና ለማስተናገድ የሚያዳግቱ በርካታ ጥያቄዎች እና ማጣጣም የሚያስፈልጉ ፍላጎቶች ይጋረጡባቸዋል ብዙ ጊዜ፣ እኒህን መሰል ጥያቄዎች እና ፍላጎቶች ማኅበረሰቦቹ ካላቸው ውሱን ሀብት እና አቅም እንዲሁም ፍላጎትን በኃይል ለማሟላት ከሚኖሩ ፍላጎቶች ጋር ተዳምረውወደ ግጭት ሲያመሩ ተስተውሏል። ይህ ዓይነቱ ክስተት እንደ ኢትዮጵያ ባሉ ታዳጊ አገሮች የተለመደ ነው።

ሆኖም ግን፣ መሰል የኃይልዕርምጃዎች ጥያቄዎች በዘላቂነት የሚፈቱበት ዘላቂ እና የተረጋጋ ማኅበረሰብ ለመፍጠር አያስችሉም። ብቸኛው የጥያቄዎቻችን ምላሽ እና ብቸኛ ዘላቂው የተለያዩ ቡድኖችን ፍላጎት ማስተናገጃ መንገድ ዲሞክራሲንማስፈን ነው።

ይህ ለምን ያሳስባል?

ለፖለቲካጥቅም ወይም ለጥያቄዎች መልስ ለማግኘት ሲባል ኃይል የመጠቀምአዝማሚያ በኢትዮጵያ የተለመደ ሆኗል። ለምሳሌ እንደ Armed Conflict Location & Event Data (ACLED) መረጃ እ.አ..አ. ከጥር 2022 እስከ ጥር 2023 ባለው ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ በአጠቃላይ 1,258 የፖለቲካ ግጭቶች የተመዘገቡ ሲሆን፣ ከእነዚህ ውስጥ ገሚሶቹ በሰላማዊ ዜጎች ላይ ያነጣጠሩ ናቸው። በእነዚህ አለመረጋጋቶች በአጠቃላይ 6,797 ሰዎች ሞተዋል።

ዲሞክራሲያዊአማራጮች ግን መሰል አደጋዎችን በማስወገድ የተለያዩ ፍላጎቶች የሚስተናገዱበት እና የተለያዩ ጥያቄዎች በአግባበቡ የሚመለሱበትን አጠቃላይ መስፈርትያስቀምጣሉ።

እርስዎ ምን ማድረግ ይችላሉ?

መረጃ ያግኙ - በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ ያሉአዳዲስ ለውጦችና ሁነቶችን በንቃት ይከታተሉ፣ የሚወሰኑ ውሳኔዎች አሳታፊነት ፣ሁሉን አቀፍነት እና የአጠቃላይ የሕዝብ ጥቅምን ማስጠበቅ ወዘገተ በመሳሰሉዲሞክራሲያዊ መርሆዎች ላይ በመመስረት ይገምግሙ።

በንቃት ይሳተፉ - በሚኖሩበት ማኅበረሰብ ውስጥ በሚከናወኑ እንደ ምርጫ፣ ሪፈረንደም፣ ዝበ ውሳኔ እና ምክክር የመሳሰሉ የውሳኔ አሰጣጥሒደቶች ውስጥ ንቁ ተሳትፎ ያድርጉ፣ ግብዓቶችን ይስጡ።

በግልፅ ይናገሩዲሞክራሲ በእርስዎ ተሳትፎ ላይ ብቻ አያበቃም። ተጠያቂነትን ማስፈን አንዱ ገፅታው ነው። ተጠያቂነት እንዲሰፍን፣ ሥጋቶችዎን መናገር እና የተሳሳቱ ድርጊቶችን መጠቆም ያስፈልጋል።

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.