ለመብትዎ ይሟገቱ! የበይነመረብ ግንኙነት ማቋረጥን ይቃወሙ!

ችግሩ ምንድን ነው?

የበይነመረብ ግንኙነትን ማቋረጥ በኢትዮጵያ እየተባባሰ የመጣ ችግር ነው። ከ2008 ወዲህ ፖለቲካዊ አለመረጋጋቶችን ተከትሎ በኢትዮጵያ ደርዘን በላይ ጊዜ የበይነመረብ ግንኙነት እንዲቋረጥ ተደርጓል። ይሁን እንጂ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጥ ጉዳይ የሚያሳስበውን ያህል ትኩረት ሊገኝ አልቻለም።

ለምን ያሳስባል?

የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጥ የዴሞክራሲና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ዕድገት ፀር ከመሆኑም ባሻገር የሰብዓዊ መብቶች እሴቶችንእና በሕገ መንግሥት የተጠበቁ የሰብዓዊ መብቶችንና ነፃነቶችን ይገፍፋል። በዓለም ዙሪያ መንግሥታት የበይነመረብን ግንኙነትን ማቋረጥ ተቃውሞዎችን ለመበተን፣ ተቃዋሚዎችን ለማፈን እና ተጠያቂነትን ለማምለጥ ተጠቅመውበታል።

የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጥ የምርጫ ተዓማኒነትን የሚያጎድል ሲሆን፣ በዚህ የዲጂታል ዘመን በይነመረብ ሲቋረጥ የሰብዓዊ መብቶችን ይገፈፋሉ። አልፎ ተርፎም የተለያዩ ዘመናዊ ንግዶችን በማደናቀፍ ኢኮኖሚው በየጊዜው በሚሊዮን ዶላሮች እንዲያጣ ያደርገዋል።  በተለይም በኢትዮጵያ የበይነመረብ ግንኙነትን ለማቋረጥ የሚያስችል ምንም ሕጋዊ መሠረት የለም። 

እርስስ ምን ሊያደርጉ ይችላሉ?

ስልታዊ ሙገታ፤ በኢትዮጵያ የበይነመረብ ግንኙነትን ለማቋረጥ የሚያስችል ምንም ሕጋዊ መሠረት ባይኖርም ቅሉ፥ ሰፊ ጉዳት እና ኪሳራ ያስከተሉ የበይነመረብ ግንኙነትን የማቋረጥ ተግባራት ግን የሐሳብን የመግለጽ እና መረጃ የማግኘት መብቶችን በማጣበብ በተደጋጋሚ ይከናወናሉ።  የሲቪልማኅበረሰብ ድርጅቶች ይህንን የመንግሥትን ሕጋዊ መሠረት የሌለው  ተግባር በፍርድ ቤት ሊሞግቱት ይገባቸዋል።

ይሳተፉ፤ካርድ በይነመረብ ላይ #KeepItOn በማለት መንግሥት የበይነመረብ ግንኙነትን ተደራሽነት ሁሌም እንዲያረጋግጥ፣ እንዲሁም #KeepItSafe በማለት ሁሉም ባለድርሻ አካላት በይነመረብ ላይ የግል ነጻነትን ከሚጋፉ እና አደገኛ ንግግሮችን ከሚያሰራጩ አካላት እንዲጠበቅ ዘላቂ ዘመቻ ያደርጋል፤ እርስዎም ከእኛ ጋር ይታገሉ።

መረጃያግኙ የበይነመረብ ግንኙነት መቋረጥ በሰብዓዊ መብቶችና በኢኮኖሚያችን ላይ የሚያስከትለውን ተፅዕኖ አስመልክቶ ካርድ ያስጠናቸውን ጥናቶች ድረገጻችን cardeth.org ላይ ይመልከቱ

RIGHTS DEPLUMED: Mapping the Human Rights Impact of Internet Shutdowns in Ethiopia

BUSINESS TRAMPLED: Demystifying the Impact of Internet Shutdown on Start-up Businesses in Ethiopia

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.