በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች - አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ ሥልጠናዎች ላይ እንዲሳተፉ የተደረገ ጥሪ

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ለ2016 'አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ' ተከታታይ ሥልጠናዎች ምዝገባ መጀመሩን ያበስራል። 'አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ' የተሰኘው የሥልጠና መርሐ ግብር በየዓመቱ በሰብዓዊ መብቶች ተሟጋችነት ለማደግ ፍላጎቱ ላላቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚመቻች ተከታታይ ሥልጠና ሲሆን፥ ወጣቶች ቀጣይ የሰብዓዊ መብቶች ውጤታማ ተሟጋች እንዲሆኑ የሚያስችላቸውን ግንዛቤ እና ክኅሎት ለማስጨበት ያለመ ነው። 

ተከታታይ ሥልጠናው የሰብዓዊ መብቶች መሠረታዊ ፅንሰ ሐሳቦችን፣ ሐሳብን የመግለጽ ነጻነት፣ የመደራጀት እና የመሰብሰብ መብቶች እንዲሁም የስርዓተ ፆታ መብቶች እና የሴቶች እኩልነት ላይ የሚያጠነጥኑ ርዕሶችን ይዳስሳል። በተጨማሪም፣ ወጣቶቹ በሰብዓዊ መብቶች ላይ ማኅበረሰባቸው ውስጥ ወይም ትምህርት ቤቶቻቸው ውስጥ የሚሠሩባቸውን እና እርስበርስ የሚገናኙባቸውን መድረኮች እንዲያገኙ ዕድል ይፈጠራል። 

የዚህ ዓመቱ 'አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ'  ተከታታይ ሥልጠና የተመቻቸው በአዲስ አበባ ለሚገኙ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነው። አመልካቾች ለሰብዓዊ መብቶች መከበር እና ለማኅበራዊ ፍትሕ ቁርጠኝነት ያላቸው መሆን ይኖርባቸዋል። 

ለመመዝገብ፣ አመልካቾች በዚህ ሊንክ የተያያዘውን ቅፅ መሙላት ይጠበቅባቸዋል። የምዝገባው የመጨረሻ ቀን እሁድ፣ ጥቅምት 11፣ 2016 ነው። 

'አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ'  ተከታታይ ሥልጠና ካርድ ሰብዓዊ መብቶችን ለማስከበር እና ለማስጠበቅ የሚያስችል ማኅበራዊ መሠረት ለመጣል የሚያደርጋቸው ሥራዎች መካከል አንዱ ነው። ካርድ ለትርፍ ያልተቋቋመ፣ መንግሥታዊ ያልሆነ፣ አገር በቀል፣ በሰብዓዊ መብቶች እሴቶች ላይ የቆመ የዴሞክራሲ ባሕል በኢትዮጵያ ሲያብብ ማየትን ራዕይ አድርጎ የሚንቀሳቀስ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ነው። 

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.