ካርድን ጨምሮ 35 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ዓመታዊ የሰላም ጥሪ አቀረቡ
የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ከሌሎች 34 አገር በቀል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ጋር በመሆን ለአዲሱ የ2016 ዓመት የሰላም ጥሪ አቅርቧል።
የሰላም ጥሪ በየዓመቱ ጳጉሜ ሲደረግ ይህ ሦስተኛው ሲሆን የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ስብስቡ በ2013 እና 2014 ጳጉሜ ወር ላይ ተመሳሳይ ይዘት ያላቸው የሰላም ጥሪዎችን አቅርበው ነበር። በዚህ ዓመቱ የሰላም ጥሪ፣ ድርጅቶቹ "በግጭቶች ውስጥ ለሚሳተፉ አካላት እና ደጋፊዎቻቸው፣ ለመንግሥት ኃላፊዎች፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች፣ ለሲቪክ ማኅበራት፣ ለመገናኛ ብዙኃን እና ጋዜጠኞች፣ ለምሁራን፣ ለተፅዕኖ ፈጣሪዎች፣ ለእምነት ተቋማት መሪዎች እና ለዓለም ዐቀፉ ማኅበረሰብ" የሚከተሉትን ጥሪዎች አስተላልፈዋል፤
- ሁሉን ዐቀፍ የሰላም መድረክ እንዲመቻች፣
- በገለልተኛ ምርመራ ተጠያቂነት እንዲሰፍን፣
- ፆታዊ ጥቃቶች ተገቢው ትኩረት እንዲሰጣቸው፣
- የተጋላጭ እና ግፉአን ጥበቃ ማዕቀፍ እንዲዘረጋ፣
- ሕዝባዊ ተሳትፎ እንዲረጋገጥ፣
- የቅድመ ግጭት መጠቆሚያ እና መከላከያ ስርዓት እንዲኖር፣
- የሰብዓዊ ድጋፍ ሳይተጓጎል እንዲቀጥል፣
- የጥላቻ ንግግር እና የተዛቡ መረጃዎች ስርጭት እንዲቆም፣
- የሲቪክ ምኅዳሩ ጥበቃ እንዲደረግለት፣ እና
- ባለድርሻ አካላት ለሰላም ግንባታ የበኩላቸውን እንዲወጡ።
የሰላም ጥሪው ሙሉ ዝርዝር እዚህ ይገኛል።
Comments (0)
Add new comment