ካርድ በዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግጭት ጉዳይ ውይይት አደረገ
ካርድ ‘በናሽናል ኢንዶውመንት ፎር ዲሞክራሲ’ ድጋፍ በዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ግጭት ጉዳይ ውይይት አደረገ። ጥር 3፣ 2012 በኢንተርኮንቲኔንታል ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ እያንሰራራ ባለው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ግጭት ዙሪያ መነሻውን እና መከላከያ መንገዶችን ታዳሚዎቹ ተወያይተውባቸዋል። ውይይቱ ላይ ተማሪዎች፣ መምህራን፣ የዩኒቨርሲቲዎች አስተዳደር ሠራተኞች ሌሎችም የሚመለከታቸው አካላት ተገኝተውበታል።
የመድረክ ተወያዮቹ “በብዙኀነት አስተዳደር” ላይ የዶክትሬት ጥናታቸውን በአዲስ አበባ እያደረጉ ያሉት የጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ መምህር መስፍን ማናዜ፣ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የሰላምና ደኅንነት ተቋም የዶክትሬት ዲግሪያቸውን እየሠሩ ያሉት አወት ሓለፎም እና በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሦስተኛ ዓመት የፖለቲካል ሳይንስ ተማሪ የሆነችው ቦንቱ አጀማ ነበሩ። ሦስቱም የተለያዩ ንጥረ ሐሳቦችን ያቀረቡ ሲሆን ከታዳሚዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎችም መልስ ሰጥተዋል።
የውይይቱን ሙሉ ሽፋን ከታች አሻም ቲቪ እንዳቀረበው ይመልከቱ!
Add a review