Skip to main content

ካርድ "የ2015 የሲማድ ሳምንት" ላይ የተሳትፎ እና የዘመቻ መርሐ ግብር እያደረገ ነው

የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ከግንቦት 30 እስከ ሰኔ 2፣ 2015 በጊዮን ሆቴል እየተካሔደ ያለው የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች (ሲማድ) ሳምንት ዐውደ ርዕይ ላይ ተሳትፎ እንዲሁም ዘመቻዎችን እያደረገ ይገኛል።  የዚህ ዓመት የሲማድ ሳምንት መሪ ቃል "ንቁ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ለዘላቂ ሰላም፣ ሰብዓዊ መብቶች እና መልካም አስተዳደር" የሚል ነው።

የሲማድ ሳምንት የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች በአንድ መድረክ ተሰብስበው ሥራዎቻቸውን ለተመልካች የሚያቀርቡበት እና በየዓመቱ የሚሰናዳ ሲሆን፣ የዘንድሮው ሦስተኛው መድረክ ነው። በመድረኩ የተለያዩ ሥነ ስርዓቶች፣ ባዛሮች፣ የውይይት እና የሚዲያ መድረኮች ይዘጋጃሉ። የሲማድ ሳምንት የሚዘጋጀው ሁሉም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች አባል በሆኑበት እና በሕግ በተቋቋመው፣ የሴክተሩ ወካይ የኢትዮጵያ ሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ምክር ቤት እና የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ትብብር ነው። ካርድ በሲማድ ሳምንት ላይ ተሳታፊ ሲሆን ይህ የመጀመሪያው ነው። 

በ2015 ሲማድ ሳምንት ላይ፣ ካርድ የማዕከሉን ሥራዎች የሚያስተዋውቁ እንዲሁም በዲጂታል መብቶች እና በዴሞክራሲያዊነት ዙሪያ የሚያተኩሩ የአድቮኬሲ ዘመቻ አዘል ኅትመቶችን ለጎብኚዎች ያሰራጫል። 

ካርድ በሐምሌ 17፣ 2011 ሕጋዊ ዕውቅና ካገኘ በኋላ ባሉት አራት ዓመታት የሠራቸውን ሥራዎች በወፍ በረር የሚያስቃኘው "የረዥሙ ጉዟችን ጅማሬ" የተሰኘ ኅትመት ሊንኩን በመከተል ማውረድ ይቻላል። 

ካርድ በ2015 የሲማድ ሳምንት የሚገኝበት መስኮት ቁጥር  52 ነው። 

Share this post

Comments (0)

Add new comment

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.