Skip to main content

ካርድ ዓለም ዐቀፍ የሰብዓዊ መብቶች ቀንን በደማቅ ክብረ በዓል በማስታወስ ዋለ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ - እሁድ፣ ሕዳር 30፣ 2016 የመብቶች እና ሞክራሲ ድገት ማዕከል (ካርለም ቀፍ የሰብዊ መብቶች ቀንን ምክንያት በማድረግ ደማቅ የሰብዊ መብቶች ክብረ በዓል በአዲስ አበባ ካፒታል ሆቴል አከናውኗል። ከቲፍቱንግ ሜንሽንረሽተ፣ ከጀርመን ኤምባሲ እና የኢትዮጵያ ሰብዊ መብት ድርጅቶች ህብረት (ኢሰመድህ) ጋር በተዘጋጀው በዚህ የሰብዓዊ መብቶች ክብረ በዓል ላይ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች እና መጪዎቹየሰብዊ መብቶችተሟጋቾች ትውልድ መካከል የትስስር መድረክ ተፈጥሯል

በኢትዮጵያ የጀርመን ፌዴራላዊ ሪፐብሊክ አምባሳደር ቴፋን ር በቁልፍ መልዕክታቸው የሰብዊ መብቶችን ሁኔታ ማሻሻል አገራዊ  መረጋጋትን እና ብልፅግናን ለማምጣት ወሳኝ ቅድመ ሁኔታዎች መሆናቸውን ተናግረዋል። በተጨማሪም አምባሳደሩ በክብረ በዓሉ ላይ ለሰብዊ መብቶች ተሟጋቾቹ እንደተናገሩት “ጀርመን ከኢትዮጵያ የሰብዊ መብት ተሟጋቾች ጎን በፅናት ትቆማለች። የካርድ ዋና ዳይሬክተር በፍቃዱ ይሉ ባደረጉት የአቀባበል ንግግር መጪዎቹ የሰብዊ መብቶች ተሟጋች ትውልድ በኢትዮጵያ ያለውን የሰብመብቶች አጠባበቅ ሁኔታ አሁን ሉት እና የቀደሙት ትውልዶች ከሞከሩት በተሻለ ሁኔታ እንደሚያንቀሳቅሱ ያላቸውን እምነት ገልጸዋል።

ቲፍቱንግ ሜንሽንረሽተ (የሰብዓዊ መብቶች ፋውንዴሽን) በተገኘ የገንዘብ ድጋፍ በካርድ አማካይነት መሠረታዊ የሰብዓዊ መብቶች ሥልጠና የወሰዱ 191 የአዲስ አበባ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ተማሪዎች “አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ” ተብለው ተሰይመዋል።  እነዚህ ወጣት መሪዎች በማበረሰባቸው ውስጥ የሰብዊ መብቶችን እሴቶችን በማስተዋወቅ እና ለሰብዊ መብቶች እና የዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ ሕዝባዊ መሠረት በመሆን ወሳኝ ሚና ይጫወታሉልጠናው የተሳተፈችው የፋውንቴን ኦፍ ኖውሌጅ ትምህርት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪዋ ዮስቲና ሰለሞን ከልጠናው በኋላ በትምህርት ቤቷ የስርዓተ ታ እኩልነት እና የሰብአዊ መብቶች ብ በመምህራኖቿ ድጋፍ አቋቁማለች። ክለቡ አሁን ከ30 በላይ አባላትን ማፍራቱን ለታዳሚዎቹ ተናግራለች።

በዘጠኝ ዙር በተደረገው ሥልጠና ድኅረ ምዘና ወቅት ጥሩ ውጤት ያስመዘገቡ ዘጠኝ ተማሪዎች ደማቅ የሰብ መብቶችጥያቄና መልስ ውድድር ላይ በመሳተፍ ውቀታቸውን እና ለሰብ መብቶች ያላቸውንፍቅር አሳይተዋል።ሦስ ዙር በተካሔደው የሰብ መብቶች ጥያቄና መልስ ውድድር ባምላክ ማተቤ ከሬኔሳንስ ኢንተርናሽናል ትምህርት ቤት 12ተኛ ክፍል ተማሪ፣ ሳሮን ተዘራ ካቴድራል ትምህርት ቤት የ11ኛ ክፍል ተማሪ፣ እና ሊዲያ ጌታሁን የኢትዮ ዌልስ ግሎባል አካዳሚ የ9ኛ ክፍል ተማሪ፣ ከአንድ እስከ ሦስተኛ በመውጣት የላፕቶፕ፣ ታብሌት እና ስልክ ተሸላሚ ሆነዋል። 

ከዚህ ትይዩ በተካሔደው የመድረክ ውይይት፣ የሰብዓዊ መብቶች ድርጅቶች በወቅታዊው ኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ሥራ ላይ ያሉ ተግዳሮቶች እና መውጫ መንገዶች ላይ ሐሳባቸውን አቅርበዋል።  ተወያዮቹ ያሬድ ኃይለማርያም (የኢትዮጵያ ሰብዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል ዋና ዳይሬክተር)፣ ስኂን ተፈራ (የሴታዊት ፌሚኒስት ንቅናቄ ዋና ዳይሬክተር)፣ ሜሮን ተስፋዬ (የሕግ ባለሙያዎች ለሰብዓዊ መብቶች ተወካይ) ናቸው። በውይይት መድረኩ ላይ አቶ ያሬድ በኢትዮጵያ የሰብዊ መብቶች ተሟጋቾች ከሚገጥሟቸው ፈተናዎች መካከል የዘፈቀደ እስራት አንዱ መሆኑን ገልጸዋል። እ.ኤ.አ. በ2023 ብቻ ከ50 በላይ የሰብዊ መብቶች ተሟጋቾች በኢትዮጵያ ውስጥ ታስረው እንደነበርም አክለው ገልጸዋል። በውይይቱ ላይ የተሳተፉት የሰብዓዊ መብቶች ተቋማት እና የሰብዊ መብቶች ተሟጋች አባላት በጉዳዩ ላይ ጥያቄዎችን በማንሳት እና አስተያየቶችን በመስጠት ንቁ ተሳትፎ አድርገዋል። 

ውይይቶቹ ባሻገር ስምንት የሰብዊ መብቶች ድርጅቶች፣ ማለትም የኢትዮጵያ ሰብ መብቶች ጉባዔ (ኢሰመጉ )፣ የኢትዮጵያ ሰብ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከልየኢትዮጵያ ባለሙያ ሴቶ ማህበር፣ ሴታዌት ንቅናቄ፣ ስብስብ ለኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች፣ የሕግ ባለሙያዎች ለሰብአዊ መብቶችCEHRO ና ካርድ፣ ከክብረ በዓሉ ጎን ለጎን በተሰናዳው ዐውደ ርዕይ ላይ በመሳተፍ ሥዎቻቸውን ለማሳየት እና ከክብረ በዓሉ ተሳታፊዎች ጋር ለመገናኘት ችለዋል። ዐውደ ርዕዩ የእርስ በርስ ትብብርን ከማጎልበቱም ባሻገር በኢትዮጵያ የሰብዊ መብቶችተሟጋቾችን ትስስር ያጠናክራል። ከኤግዚቢሽኑ ተሳታፊዎች መካከል የተሟጋቾች ማዕከሉ በ12 ዩኒቨርሲቲዎች እንዲቋቋም የረዳቸውን የሰብዊ መብቶች ክለቦች አስተዋውቋል፤ ይህም የሥልጠናው ተጠቃሚ የሆኑት ተማሪዎች ወደ ዩኒቨርሲቲ ሲገቡ መጀመሪያ የሚስተናገዱበትን ከመደበኛ ትምህርት ተጓዳኝ ያለ ክበብ ያሳውቃቸዋል። 

የሰብዊ መብቶች ክብረ በዓሉ ስኬቶችን ለማክበር፣ ተግዳሮቶችን ለመፍታት እና የወደፊቷን የሰብዊ መብቶች ተሟጋቾችን በኢትዮጵያ ለማብቃት እንደ ሁነኛመድረክ ሆኖ አገልግሏል። ክብረ በዓሉ ካር ለሁሉም ፍትዊ የሆነ ዴሞክራሲያዊ ባሕል እና ስርዓት ለመገንባት ያለውን ቁርጠኝነት አሳይቷል።

በክብረ በዓሉ መዝጊያ ላይ የካርድ ፕሮግራም ዳይሬክተር አጥናፉ ብርሃኔ፣ አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ትውልድ አባላቱ "ለሰብዓዊ መብቶች በጋራ እንቆማለን" የሚለውን ቃለ መሐላቸውን ተቀብለዋቸዋል።

የዘንድሮው የሰብዊ መብቶች ክብረ በዓል በተከታታይ ከተደረጉት ክብረ በዓሎች ሦስተኛው ሲሆን ካር እስካሁን ተመሳሳይ ልጠና የሰጣቸው እና አዲስ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋች ትውልድ ብሎ የሰየማቸው ተማሪዎች ቁጥር በአጠቃላይ 925 አድርሶታል።  ክብረ በዓሉን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ፣ አርትስ ቴሌቪዥን እና አዲስ አበባ ሚዲያ ኔትወርክን ጨምሮ በርካታ ሚዲያዎች ለክብረ በዓሉ የሚዲያ ሽፋን ሰጥተውታል።

Share this post

Comments (0)

Add new comment

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.