ካርድ 'ቴክኖሎጂ ያመጣው ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት' የሚዳስስ ጥናት ይፋ ማድረጊያ ዐውደ ርዕይ ላይ ተሳተፈ
የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ሴንተር ፎር ኢንፎርሜሽን ሪዚሊየን (CIR) የተባለ ዓለም ዐቀፍ ተቋም፣ በኢትዮጵያ 'ቴክኖሎጂን ያመጣው ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት' የሚዳስስ ጥናት ይፋ ማድረጊያ መርሐ ግብርን፣ ከኢትዮጵያ የሰብዓዊ መብቶች ተሟጋቾች ማዕከል (EHRDC) ጋር በመሆን ትላንት፣ ግንቦት 1፣ 2016፣ በኤሊያና ሆቴል የተዘጋጀው ዐውደ ርዕይ ላይ ተሳትፎ አድርጓል።
ካርድ በዲጂታል መብቶች ፕሮግራሙ ሥር ፍትሐዊ የበይነመረብ ተደራሽነት እንዲስፋፋ እና የበይነመረብ ተጠቃሚዎች ደኅንነት እንዲረጋገጥ የሚያስችሉ ሥራዎችን ይሠራል። ካርድ በዐውደ ርዕዩ ላይ ተሳትፎ ሲያደርግ ቴክኖሎጂ ያመጣው ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት ለበይነመረብ ተጠቃሚዎች ደኅንነት ዋነኛ ስጋት መሆኑን ስለሚያምን ነው።
ካርድ በተከታታይ ዘመቻ ከሚያደርግባቸው ጉዳዮች መካከል፣ #KeepItSafe በሚል ሀሽታግ ሥር መንግሥት እና ማኅበራዊ ሚዲያዎችን ጨምሮ፣ ሁሉም ባለድርሻ አካላት፣ የበይነመረብ ተጠቃሚዎችን ደኅንነት እንዲጠብቁ መሟገት አንዱ ነው። ለዚህ ዐውደ ርዕይ ሲባል፣ ካርድ በይነመረብ ላይ በሠራው ሰርቬይ እንደተረዳው 78% የሚሆኑት እና ቴክኖሎጂ ላይ ፆታን መሠረት ያደረገ ጥቃት የደረሰባቸው ሴቶች፣ ጥቃቱን ሪፖርት አያደርጉም።
ከሰርቬዩ በተጨማሪም፣ ካርድ ቴክኖሎጂ ያመጣው ፆታዊ ጥቃትን ለመረዳት እና ለመመከት የሚያስችል መረጃ የያዘ ብሮሸር ለታዳሚዎች አከፋፍሏል።
በዐውደ ርዕዩ ላይ፣ የካርድ ተሳትፎ፣ ድርጅታችን ለዲጂታል መብቶች እና ደኅንነት ያለውን ቁርጠኝነት የሚያሳይበት ነው። የሰርቬዩ ግኝትም ቴክኖሎጂ ያመጣቸው ፆታዊ ጥቃቶች እምብዛም ሪፖርት እንደማይደረጉ በማሳየቱ የሁላችንንም ርብርቦሽ የሚጠይቅ ሥራ ከፊታችን እንደተደቀነ ማስታወሻ ነው
Add a review