Skip to main content

ባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ካርድን ከሥራው አገደ

አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ – ሕዳር 3፣ 2017 በተጻፈ ደብዳቤ የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ከሥራ እንዲታገድ ወስኗል። እግዱ በማስረጃ ያልተደገፉ "ፖለቲካዊ ገለልተኛ አለመሆን" እና "የአገር ጥቅም የሚጎዳ ሥራ ላይ መሠማራት" የሚሉ ምክን ያቶችን ያዘለ ነው። 

ካርድ ይህንን ክስ በፅኑ የሚቃወም ሲሆን፣ ለግልጽነት፣ ለገለልተኝነት እና ዴሞክራሲያዊነት ያለውን ቁርጠኝነት በመግለጫው በማረጋገጥ፣ ድርጅቱ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩ እና ዴሞክራሲያዊ ባሕል እንዲገነባ መሠረት የሚጥሉ ሥራዎችን ዕውቅና ካገኘበት ጊዜ ጀምሮ እየሠራ መቆየቱን ተናግሯል። 

እግዱን በተመለከተ፣ ካርድ ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ጋር ንግግር ለማድረግ እየሞከረ ሲሆን፣ ባለሥልጣኑ ውሳኔውን በድጋሚ እንዲያጤነው ጠይቋል። ካርድ እግዱ እንዲነሳ ሁሉንም ሕጋዊ መሠረት ያላቸው መንገዶች በሙሉ አሟጦ ይጠቀማል። 

ሙሉውን የካርድ መግለጫ እዚህ ማንበብ ይቻላል።

Share this post

Comments (0)

Add new comment

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.