Update on the Lifting of Suspension of CARD
በመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) ላይ ተጥሎ የነበረው የዘፈቀደ ዕገዳ ስለ መነሣቱ ለማሳወቅ የተሰጠ መግለጫ
ታኅሳስ 3 ቀን 2017
አዲስ አበባ
የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ምዕከል (ካርድ) ኅዳር 03 ቀን 2017 በሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ተጥሎበት የነበረው የዘፈቀደ ዕገዳ ትላንት ታኅሳስ 02 ቀን 2017 ጀምሮ መነሣቱን ለማሳወቅ ይወዳል። የዘፈቀደ ዕገዳውን የማንሣት ውሳኔ የተላለፈው ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች ጋር ችግሩን ለመፍታት ካደረግናቸው ከፍተኛ እና ተደጋጋሚ ጥረቶች በኋላ ነው።
ድርጅታችን ሕጋዊ ሂደቶችን በመከተል የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ለምርመራ ለላካቸው የክትትል እና ግምገማ ቡድን አባላት ሙሉ ትብብር ያደረገ ሲሆን ባለስልጣኑ ከእገዳው መነሣት ጋር ተያያዞ ለካርድ የማስጠንቀቂያ ደብዳቤ ሰጥቷል። በማስጠንቀቂያ ደብዳቤው ላይ ጥሰት ናቸው ተብለው የተቀመጡትን ነጥቦች አስመልክቶ ከባለሥልጣን መሥሪያ ቤቱ እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው ሌሎች አካላት ጋር የምናደርገውን ውይይት በመቀጠል ምላሽ የሚሹ ጥያቄዎቻችንን ለመፍታት እንደምንጥር እያሳወቅን ወደ መደበኛ ሥራችን መመለሳችንን ለመግለጽ እንወዳለን።
በዚህ አስቸጋሪ ጊዜ ድጋፋችሁን ለሰጣችሁን፣ አብራችሁ ለቆማችሁ እና ድምጽ ለሆናችሁን የካርድ ቤተሰቦች እና ወዳጆች የላቀ የአጋርነት ምስጋናችንን እናቀርባለን።
በአብሮነት፣
የመብቶች እና ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ)
Comments (0)
Add new comment