ካርድ ከዳታ ፎር ቼንጅ ጋር በመተባበር የሁለት ሳምንታት የበይነመረብ ዘመቻ በበይነመረብ ተዳራሽነት ላይ ማድረግ ጀመረ

የመብቶች እና  ዴሞክራሲ ዕድገት ማዕከል (ካርድ) በ“ዳታ ፎር ቼንጅ” የውሂብ ትንታኔ (ዳታ አናሊሲስ) ፌሎሺፕ እና የውሂብ-ተረክ (ዳታ ስቶሪ) ዝግጅት አቅም ማሳደጊያ ድጋፍ በመቀበል በበይነመረብ ላይ የሚካሔድ እና ለሁለት ሳምንታት የሚቆይ የበይነመረብ ተዳራሽነትን መስፋፋት የሚጠይቅ ዘመቻ፣ በበይነመረብ ላይ ጀመረ።

የበይነመረብ ዘመቻው “የዲጂታል ክፍፍል፤ የበይነመረብ ተዳራሽነት መጓደል የኢትዮጵያ አቅም ላይ የጣለው እንቅፋት” በሚል ርዕስ የሚደረግ ሲሆን፥ በመረጃ ላይ የተመሠረተ በኢትዮጵያ ያለውን የዲጂታል ክፍፍል - ማለትም በበይነመረብ ተጠቃሚዎች እና ተጠቃሚ ያልሆኑ ዜጎች መካከል ያለውን ሁለገብ አቅምን ለመጠቀም ያላቸውን የዕድል ልዩነት - ያሳያል። ይህ ዘመቻ፣ በመሠረተ ልማት አለመስፋፋት፣ በዋጋ ውድነት፣ እና በመንግሥት ማዕቀብ ምክንያት የዲጂታል ክፍፍሉ ሰፊ መሆኑን እና ኢትዮጵያውያን በበይነመረብ ተዳራሽነት ከአፍሪካ አማካይ በታች መሆናቸውን በማሳየት ነገር ግን መንግሥት በዕቅዱ መሠረት ከሚያልመው ተቃራኒ መሆኑን ለማሳየት ያስችላል። የበይነመረብ አገልግሎት ዋጋ ተመጣጣኝ መሆን እና የተዳራሽነቱ መሥፋፋት ለሕዝቦች የነፍስ ወከፍ ገቢ መጨመር ይረዳል።

ዘመቻው በፌስቡክ፣ በትዊተር፣ በኢንስታግራም እና በቴሌግራም በአማርኛ፣ በእንግሊዝኛ እና በኦሮምኛ ይካሔዳል። ካርድ በበይነመረብ ተዳራሽነት አስፈላጊነት የሚያምኑ ግለሰቦችንም ይሁን ድርጅቶችን ዘመቻችንን #KeepItOn የሚል ሀሽታግ በመጠቀም እንዲቀላቀሉ እንጋብዛለን።  

የውሂብ-ተረካችንን እዚህ ያንብቡ!

The campaign uses data-based evidence to showcase the wide gap between the reality on the ground and the ideal where the Ethiopian government envisions seeing progress in improving digital access. Poor infrastructure, unaffordable tariffs, and government-imposed shutdowns of the Internet's accessibility are among the contributors to the digital divide, the gulf between those who have ready access to the internet and those who do not, in Ethiopia. The storyline also demonstrates how the GDP per capita of Ethiopia will benefit from increased accessibility and affordable internet tariffs.

The campaign will run on Facebook, Twitter, Instagram, and Telegram with messages in English, Amharic, and Afaan Oromoo languages. CARD invites every person or organization that believes in the vital role of internet access to explore Ethiopia's potential, please share its story using the #KeepItOn hashtag.

Read the story now!

Add a review

The comment language code.

Restricted HTML

  • Allowed HTML tags: <a href hreflang> <em> <strong> <cite> <blockquote cite> <code> <ul type> <ol start type> <li> <dl> <dt> <dd> <h2 id> <h3 id> <h4 id> <h5 id> <h6 id>
  • Lines and paragraphs break automatically.
  • Web page addresses and email addresses turn into links automatically.